Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

ግልጽ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 386

ግልጽ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 386

Description

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ፡ አቢሲንያ ባንክ አ.ማ.

 

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ለሰጣቸው ብድሮች በመያዣነት የያዛቸውን ቤቶች በድጋሚ በግልፅ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ ነው።


 

1. በሐራጅ የሚሸጡ ንብረቶች ዝርዝር

 

ተ.ቁ የተበዳሪው ስም የመያዣ ሰጪው ስም የንብረቱ አይነት እና አገልግሎት የቦታው ስፋት (ካ.ሜ) ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ የጨረታው መነሻ ዋጋ (ብር) ጨረታው የሚካሄድበት ቀን የምዝገባ ሰዓት የጨረታ ሰዓት
1 ሚልቶ ጀነራል ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር አቶ አበበ ሰቦቃ መኖሪያ ቤት 416 ሸገር ከተማ፣ መነአቢቹ ክ/ከተማ፣ ቱፋ ሙና ወረዳ (በቀድሞ ሱሉልታ ከተማ) 12,722,968.85 ህዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም 4:30-5:30 5:30-6:00
2 ሚልቶ ጀነራል ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር አቶ አበበ ሰቦቃ መኖሪያ ቤት 500 ሸገር ከተማ፣ መነአቢቹ ክ/ከተማ፣ ቱፋ ሙና ወረዳ (በቀድሞ ሱሉልታ ከተማ) 7,589,729.97 ህዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም 8:30-9:30 9:30-10:00
3 ሚልቶ ጀነራል ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር አቶ አበበ ሰቦቃ መኖሪያ ቤት 200 ሸገር ከተማ፣ መነአቢቹ ክ/ከተማ፣ ቱፋ ሙና ወረዳ (በቀድሞ ሱሉልታ ከተማ) 5,771,383.60 ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም 4:30-5:30 5:30-6:00
4 ሚልቶ ጀነራል ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር አቶ አበበ ሰቦቃ መኖሪያ ቤት 300 ሸገር ከተማ፣ መነአቢቹ ክ/ከተማ፣ ቱፋ ሙና ወረዳ (በቀድሞ ሱሉልታ ከተማ) 5,414,918.36 ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም 8:30-9:30 9:30-10:00

 

የጨረታ ቦታ

 

  • አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 7 ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠር እና ዴት ሊቲጌሽን ዲቪዥን የጨረታ ክፍል ውስጥ ነው።

 

2. የሐራጅ ደንቦች

 

  1. የጨረታ ማስያዣ (ሲፒኦ):
    • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ)አቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም የተሰራ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው።
  2. ክፍያ እና ቅጣት:
    • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አጠቃሎ መክፈል አለበት።
    • በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ ለባንኩ ገቢ ይሆናል
    • በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል
  3. የግብር እና ክፍያዎች:
    • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ (የሚከፈልበት ከሆነ) እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል
    • ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን፣ ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ግን ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል
  4. ብድር አቅርቦት:
    • በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ/አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል
  5. መገኘት:
    • ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀን እና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል
  6. ንብረት መጎብኘት:
    • ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
  7. የባንኩ መብት:
    • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

3. የእውቂያ መረጃ (ለተጨማሪ መረጃ)

 

  • ስልክ ቁጥር: 0115 15 11 53 እና 0115 15 07 11
  • አድራሻ: አዲስ አበባ

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.