Search
Add Listing
  • You have no bookmark.

Your Wishlist : 0 listings

Sign In

ግልጽ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 396

ግልጽ ጨረታ

Now Open
  • Viewed - 396

Description

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ የሰጠው ብድር ባለመከፈሉ በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) 216/92 መሠረት በእዳ ማካካሻት የወረሳቸውን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

1. በሐራጅ የሚሸጡ ንብረቶች ዝርዝር

 

ተ.ቁ የተበዳሪው ሙሉ ስም የመያዣ ሰጭው ስም የንብረቱ አይነትና አገልግሎት የቦታው ስፋት (ካ.ሜ) ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ የጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር) ጨረታ የወጣበት ጊዜ
1 ሲትረስ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ መስከረም ታደሰ የንግድ ቤት 2600 ኦሮሚያ ክ/መ፣ ሰንዳፋ በኬ ከተማ 9,998,261.35 ለመጀመሪያ ጊዜ
2 ጂዲ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ደጀኔ ሞገስ መኖሪያ ቤት 302 አ.አ ከተማ የካ ክ/ከ ወረዳ 13 28,102,022.43 ድጋሚ
3 ኢዩኤል ሰለሞን ተበዳሪው ጅምር መኖሪያ ቤት 160 ኦሮሚያ ክ/መ፣ ሰንዳፋ በኬ ከተማ 1,422,740.65 ለመጀመሪያ ጊዜ
4 ዳንኤል መብራቱ ተበዳሪው መኖሪያ ቤት 400 ኦሮሚያ ክ/መ፣ መተሐራ ከተማ 709,845.00 በድጋሚ
5 ክንዱ አለበል ተበዳሪው መጋዘን 5000 አማራ ክ/መ፣ ገንደውሃ ከተማ 12,528,675.00 በድጋሚ
6 ብርሐኑ በየነ ተበዳሪው መኖሪያ ቤት 500 ሲዳማ ክ/መ፣ ቱላ ከተማ ቀበሌ 01 2,267,325.00 በድጋሚ
7 ጉንሳሞ ጉጋ ተበዳሪው መኖሪያ ቤት 436.6 ሐዋሳ ጩኮ ክ/ከተማ 315,000.00 በድጋሚ
8 ወይ. የሰውዘር አዝመራው ተበዳሪው መኖሪያ ቤት 250 አማራ ክ/መ፣ ሞጣ ከተማ 1,152,510.00 በድጋሚ
9 እስክንድር አስራት ተበዳሪው መኖሪያ ቤት 150 አማራ ክ/መ፣ አዴት ከተማ 943,662.13 በድጋሚ
10 ኢብራሂም መሀሐመድ ኑር ይድነቃቸው መንበሩ ሆቴል 820 ኦሮሚያ ክ/መ፣ ኦለንጭቲ ከተማ 16,662,424.75 በድጋሚ
11 ኢብራሂም መሀሐመድ ኑር ዮርዳኖስ ንጉሴ መኖሪያ ቤት 188 ኦሮሚያ ክ/መ፣ ኦለንጭቲ ከተማ 2,973,853.00 በድጋሚ
12 አል-ባብ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ፈትያ ነጃ የንግድ ቤት 400 ኦሮሚያ ክ/መ፣ አዳማ ከተማ 15,063,471.94 ለመጀመሪያ ጊዜ
13 ኖሐብ አሊ ተበዳሪው መኖሪያ ቤት 200 ኦሮሚያ ክ/መ፣ ሰንዳፋ በኬ ከተማ 1,753,291.70 ለመጀመሪያ ጊዜ
14 ሙባረክ ድልገባ ተበዳሪው መኖሪያ ቤት 200 ኦሮሚያ ክ/መ፣ ዶዶላ ከተማ 2,408,198.18 ለመጀመሪያ ጊዜ
15 ሲሳይ ሞሴ ላመነው ከበደ መኖሪያ ቤት 200 ሸገር ከተማ ሱሉልታ መነ አብቹ ክ/ከ አትሌት ሰፈር 8,875,095.52 ለመጀመሪያ ጊዜ
16 ጂዲ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ መሐመድኑር አሊ መጋዘን 1736 ኦሮሚያ ክ/መ፣ አዳማ ከተማ ቀበሌ 01 25,856,220.81 በድጋሚ

 

2. የጨረታው የጊዜ ሰሌዳና ቦታ

 

  • የጨረታ ቀን: ኅዳር 4 ቀን 2018 ዓ.ም
  • የጨረታ ሰዓት: ከረፋዱ 4፡30 አስከ 5፡30
  • የጨረታ ቦታ:
    1. አዲስ አበባ ከተማ ሰሜን ሆቴል ጎን በሚገኘው የባንኩ ህንጻ 6ኛ ፎቅ (የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር ቢሮ)
    2. ንብረቶቹ በሚገኙበት ዲስትሪክት ጽ/ቤቶች

 

3. የሐራጅ ደንቦች

 

  1. የጨረታ ማስያዣ (CPO):
    • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ማስያዝ አለባቸው።
  2. የጨረታ ሰነድ:
    • ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በባንኩ ቅርንጫፎችና በሰሜን ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የባንኩ ሕንጻ የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር 6ኛ ፎቅ መውሰድ ይቻላል።
  3. የዋጋ ማቅረቢያ:
    • ተጫራቾች ዋጋቸውን በጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ቅጽ ላይ ከሰፈሩ በኋላ፣ የጨረታ ማስከበሪያና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በማያያዝ በሰም በታሸገ ፖስታ ጨረታው መካሄጃ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  4. ክፍያ እና ቅጣት:
    • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ጠቅላላ ዋጋውን ከፍሎ ንብረቱን/ንብረቶቹን መረከብ ይኖርበታል። ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
    • ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል
  5. የግብር እና ወጪዎች:
    • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎች ገዢ ይከፍላል። የሊዝ ክፍያ ውል ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል
  6. ንብረት መጎብኘት: ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል
  7. ብድር አቅርቦት: መስፈርቱን ለሚያሟሉ ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል
  8. የባንኩ መብት: ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

4. የእውቂያ መረጃ

 

  • ስልክ ቁጥር: 011-126-4594 / 0918-778427
  • አድራሻ: አዲስ አበባ

Listing Locations

0
Close

Your cart

No products in the cart.