ኢትዮጵያ በአፍሪካ የባንክ ዘርፍ ተሳትፎዋን አጠናክራ ቀጥላለች። በ2025 የአፍሪካ 100 ታላላቅ ባንኮች ዝርዝር ውስጥ ስድስት የኢትዮጵያ ባንኮች ሲገቡ፣ ይህም ከ2024 (አምስት) እና ከ2022 (ሁለት) ጋር ሲነጻጸር እድገት አሳይቷል።
ይህ እድገት የሀገሪቱን የባንክ ዘርፍ የቁጥጥር ስርአት መፍታት እና ውድድር መጨመር ያመለክታል ሲል አፍሪካ ቢዝነስ ዘግቧል። አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ የላቀ እድገት በማስመዝገብ ከዝርዝሩ ጎልቶ ወጥቷል።
18 ደረጃዎችን በማሻሻል 50ኛ ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን፣ በ507 ሚሊዮን ዶላር የደረጃ 1 ካፒታል እና ወደ 12 ሚሊዮን የሚጠጉ ደንበኞች አሉትም ተብሏል።

Add Comment