ባንኩ መሰል ጨረታ ሲያወጣ ለ10ኛው ዙር ሲሆን በዚህ ዙር 150 ሚሊዮን ዶላር ነበር ያቀረበው።
በጨረታው የአንድ የአሜሪካን ዶላር አማካይ የምንዛሪ ተመን 148.1007 ብር ሆኖ ተመዝግቧል። / 1 ዶላር በ148.1007 ተሽጧል /
ይህ አዲስ አማካኝ ዋጋ ከሁለት ወራት በፊት በ9ኛው ዙር ጨረታ ከተመዘገበው 138.2 ብር አማካይ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር፣ የ9 ብር ከ90 ሳንቲም ወይም የ 7.16 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
ዛሬ በተካሄደው የውጭ ምንዛሪ ድልድል 31 ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በማግኘት ተሳክቶላቸዋል።
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ገበያው በሚፈቅደው ጊዜ ጨረታዎቹን ማካሄዱን እንደሚቀጥል አስታውቋል።
Add Comment